የሕፃንነት ኑሮ ይበቃናል
በሀይማኖት ማደግ ይገባናል
የማስመሰል ሕይወት ምን ይጠቅማል
1.
እድሜአችንን ስናይ እጅግ ገፍቷል
ቢቆጠር ከመቶም በላይ ሆኗል
ግን እንደህፃን መናገር አልተውንም
ከእንግዲህስ ይብቃን አያዋጣንም
2.
በኃይማኖት ስም ተጐናጽፈን
አለምን መስለን የኖርነው ዘመን
ምንም አልጠቀመን ይበቃናል
ባዲስ ህይወት ማደግ ይሻለናል
3.
በከንቱ ያሳለፍንበት ሰዓት
በሕይወታችን የተቃለድንበት
ያለማወቅ ወራት አሁን ይብቃን
በጌታ ይታደስ ህይወታችን
4.
ሁልጊዜ ምግባችን ወተት ሆኖ
አልወጣንም ከህፃንነት ኑሮ
እድገት በሌለው ህይወት እየኖርን
እስከመቼ በንዲህ እንዘልቃለን
5.
በወግና በባህል ተሳስረን
ባለማዊነትም አንድ ሆነን
ያሳለፍነው ዘመን ይበቃናል
ከእንግዲህ መለወጥ ይሻለናል