በጉዞ ላይ ነን ተነስተን ከአለም
ወደ አዲሲቷ አገር ወደ የሩሳሌም
መንገዱ ቢሆንም የሚያደክም
በእግ/ር ከታመንን እንገባለን
1.
ታማኙ ክርስቲያን መጓዝ አለበት
በኢየሱስ ፀሎት ብርሃን ለህይወት
ለሰዎችም ፍቅር ራሱን በመስጠት
እግ/ርን ደግሞ ደስ ለማሰኘት
2.
የእስራኤል ህዝቦች በመንገድ ላይ ሳሉ
ያረገላቸውን ፍፁም ሳይረዱ
እንዳጉረመረሙ በጐዞአቸው ሁሉ
ምድረበዳ ቀሩ በቃሉ ሳይፀኑ
3.
በዚህ ዘመን ያለህ የእግ/ር ወገን
ለእስራኤል ህዝቦች ልናገር ከማለት
በማጉረምረም ህይወት ምድረበዳ መቅረት
ዛሬም እንደነኢያሱ ወደ ከነአን መግባት
4.
መንገዱ ጠባብ ነው በእምነት ሲጓዙበት
ሸክም ተሸክመን የማንችልበት
ሸክማችንን ሁሉ እናራግፈው አሁን
ለሚያልፉትም ሰዎች እንቅፋት እንዳንሆን/2X/