እግዚአብሔርን ማግነን ማንገስ ነው ሥራዬ
በዘመኔ ሁሉ አዜምለታለሁ
ቢከፋኝም ቢደላኝም በቤቱ እኖራለሁ
1.
ኑሮ እንደሬት መሮኝ ሌተ-ቀን ሳነባ
ጉልበቴ ተሟጦ አምላኬን ስጣራ
እርሱ ሊያፅናናኝ ፈፅሞ አልዘገየም
የረዳኝ እግዚአብሔር ከፍ ይበል ዘላለም
2.
ፍርዱ እውነተኛ ቃል ኪዳኑ ፅኑ
ምህረቱ ግሩም ነው አሠራሩ ልዩ
ማስተዋል ጥበቡ እውቀቱ ጥልቅ ነው
የልቡንስ ሀሣብ ሊያውቅ የሚችል ማነው
3.
ምድር ሀሴት ታድርግ ምሥጋናዋን ታምጣ
ደሴቶችም ዛሬ ያክብሩት በእልልታ
እግዚአብሔር ነግሦ አህዛብ ደነገጡ
በጣኦት ሚመኩ እንደሰም ቀለጡ
4.
ተራሮች ቢናዱ ባህሩም ቢናወጥ
ተስፋ እንደሌለው ሰው ከቶ እኔ አልታወክ
ባምላክ አደባባይ ሁሌ እዘምራለሁ
ልክ እንደወይራ ዛፍ ለምልሜ አድራለሁ