ሁሉም ነገር ግራ ቢገባንም
በጌታ ግን ደስ ይለናል
እንባችን ጠርጐ ያፅናናል
1.
ኑሮአችን ምስቅልቅሉ ጠፍቶን
ነገር ሁሉ ግራ ተጋብቶን
ቢመስለንም ኑሮ መራራ
አንድ ቀን ያበቃል የዚህ ዓለም መከራ /2/
2.
ስንወጣ ስንገባ መከራ
ቢፈራረቅብን በተራ
በመድኃኒታችን ተስፋ አለን
እንታመናለን እስከሚመጣልን /2/
3.
ድካም ድንዛዜ ቢበዛም
የመውጫ ቀዳዳ ቢጠፋም
በሚያበረታን በጌታችን
በድል እንቆማለን በፀጋው ደግፎን /2/
4.
ጣላት ህይወታችንን ሽቶ
ሊያጠፋን ቢፈልግ በርትቶ
ጌታ ግን ቀድሞ ይደርስና
እናሸንፋለን ፊቱ ይመራንና /2/
5.
እንዳሰብነው ሳይሆን ቢቀርም
በምድር ችግሩ ቢበዛም
የሚያሳርፈን ጌታ ይመጣል
ሸክማችን ተራግፎ ሰማይ ያገባናል /2/