ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #94 / Song #94

እግዚአብሔር ሆይ ምስጉን ነህ /2x/

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ክርስቶስ ሆይ ምስጉን ነህ /2x/
በጠላት ራስ ላይ ቆምን ባናቱ ላይ
ከፍ ከፍ አረከን ጌታችን ወደ ላይ
እንደ ዓይን ብሌን ተጠንቅቀህልን
ባንተ ነው የቆምነው እንደዚህ አምሮብን
1.
ሳናክሬም ቢሮፍክር ባሮቹ ሊያደርገን
ዙሪያችንን ከቦን ጠላት ቢያስጨንቀን
}2xደብዳቤ እየጻፈ እኛን ቢያስፈራራም
ነፃ አውጪው እግ/ር ይኸው ነፃ አወጣን
2.
እሳት ወስጥ ጨምረው ቢሹም ሊያቃጥሉን
አንበሳ እንዲበላን ጉድጓድ ውስጥ ቢጥሉን
}2xበእሳት በጉድጓድ አብሮን ይቆምና
ያወጣናል የሱስ ሽፍን ያደርግና
3.
የየሱስን ማዳን ላለም እንዳንመሰክር
በሰንሰለት ታስረን ግዞት ብንጨመር
}2xየእስር ቤቱን ደጆች በጆቹ ከፋፍቶ
የሱስ ነፃ አወጣን ሰንሰለቱን ፈትቶ
4.
ጠላት ሊያዋርደን በብርቱ ፈልጐ
ሊውጠን ቢመኘን ጓግቶና ጐምጅቶ
}2xከጠላት ንክሻ ጌታችን ጠበቀን
ወጥመዱ ተሰብሮ እኛም አመለጥን
100%
100%