ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #159 / Song #159

ማነው በዚህ ዘመን ነህሚያ /2X/

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ማነው በዚህ ዘመን ነህሚያ /2X/
ለህዝብህ የሚቆም ታማኝ ባሪያ
ማነው በእኛ ዘመን ነህሚያ
1.
የፈረሰውን ቅጥር የሚያነሳ
የጠፋውንም በግ የሚያመጣ
ኃጢያትን በስሙ የሚጠራ
ማነው በዚህ ዘመን ነህሚያ
2.
ለነፍሳት የሚያለቅስ ጠዋት ማታ
አንዴም ሳያቋርጥ የሚተጋ
በቃልም የሚቆም እውነተኛ
ዛሬም አስነሣልን አባ ለኛ
3.
የወገኑን ሸክም የሚሸከም
እራሱን ዝቅ አርጐ የሚያገለግል
ደካማውን በቃልህ የሚያቀና
ስጠን አባት ለእውነት የሚቀና
4.
ለጠላቱ ትጥቁን የማይፈታ
በባዕድ ጭፍሮች ላይ የበረታ
በጉልበቱ ሚሄድ ታማኝ ባሪያ
አስነሳልን ጌታ ነህሚያ
100%
100%