ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #53 / Song #53

ለተጠማ ሁሉ ሚዳረስ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የሚያረካ የሕይወት ምንጭ የሱስ
ኑና በነፃ ጠጡ ይላል
ለፈለገ ሁሉ ያዳርሳል
1.
የሕይወት ውሃ የጠማችሁ
የሕይወት ምግብ የራባችሁ
ለዘላለም የሚያረካውን
ኑና ቅመሱት ኢየሱስን
2.
ለተራበ ሁሉ ሚዳረስ
የሕይወት እንጀራ ኢየሱስ
ኑና በነፃ ብሉ ይላል
ሳይለያይ ሁሉን ያዳርሳል
3.
በነፍሳችሁ ለጠወለጋችሁ
በመንፈስም ለደረቃችሁ
ልምላሜውን ሊሰጣችሁ
ኑና እረፉ ይላል ጌታችሁ
4.
መዳናችሁን ፈልጋችሁ
ምትጨነቁ ለነፍሳችሁ
መዳን በሌላ የለምና
እረፉ በጌታ እመኑና
100%
100%