ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #52 / Song #52

አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
በተቀደሰው ተራራ ላይ ማን ይኖራል
1.
በቅንነት መንገድ የሚሄድ
እውነተኛውን ጽድቅ የሚያደርግ
የልቡንም ሀሣብ ሚያቀና
ይህን የሚያደርግ የት አለና
2.
እውነትን እውነት ነው የሚላት
ሀሰትን ከልቡ ሚያርቃት
ጌታ እንደሚወደው የሚኖር
እውነተኛ ቃሉን ሚናገር
3.
ባንደበቱ የማይሸነግል
በባልንጀራው ላይ የማይፈርድ
ቅዱስ እግ/ርን የሚፈራው
ለርሱ ነው ሚሰጠው ተራራው
4.
በእጃቸው ቃሉን የያዙ
በእውነተኛ መንገድ የተጓዙ
ጌታ እነዚህን ጠርቷቸዋልና
መንግሥቱም ለነዚህ ናትና
5.
የእግ/ር ከተማ ቅዱስ ነው
እኛም የምንገባው ወደዚያ ነው
ተራራውን ሊያወርሰን ጠርቶናል
ደስታችንም እጅግ ከፍ ብሏል
100%
100%