ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #50 / Song #50

አካሄዴ ተበላሽቶ እንደመንገድህ ባልሄድም

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ባመጽ ክፋት ተሞልቼ ዘውትር ባሳዝንህም
ወደ ሕይወት ስትመራኝ እኔ ግን ሞትን ብመርጥም
አመሠግናለሁ ጌታ ከእጆችህ አልጣልከኝም
1.
ከእጆችህ አልጣልከኝም ኃጢያቴን ሁሉ እያየህ
ለምህረትህ የምትቸኩል ነህ ለቁጣ ግን የዘገየህ
እስካሁን ድረስ መኖሬ በሥራዬ አይደለምና
ለፍጥረታት ሁሉ ጌታ ይድረስህ ታላቅ ምሥጋና
2.
በእይኖችህ የማያምር ብልሹ ነው አካሄዴ
ወደ ሲኦል የሚወስደው እጅግ ሠፊ ነው መንገዴ
የዘላለም የሞት ጉዞ ሆኖ ሳለ ጐዳናዬ
ነፍሴ ባንተ ከሞት ዳነች ተመስገንልኝ ጌታዬ
3.
ምንም ተስፋ የሌለኝ ሰው የሞት የጥፋት ጓደኛ
በድቅድቅ ጨለማ ስኖር ያለ አንዳች ምንም እረኛ
ኢየሱስ የሚባል ጌታ ይህን እዳ ከፈለልኝ
እኔ መሰቀል ሲገባኝ እርሱ ግን ተሰቀለልኝ
4.
ዓለም ተስፋሽን ቁረጭ ከአንግዲህ የየሱስ ነኝ
ጌታ በፀጋው አድኖኝ በምህረቱ ወሰደኝ
በክንፎቹ ተማምኜ በአምላክ ጥላ ሥር ስላለሁ ኃይልን በሚሰጠኝ ጌታ ሁሉን ነገር እችላለሁ
100%
100%