ያምልኮ የዝማሬ ድምፅ ከቶ ማይሰማ
ለምሥል ሰግጄ ከምኖር በሠላም
አምላኬን አክብሬ ይሻላል ብሰዋ
1.
ውሣኔህን አድርግ ክርስቲያን ወገኔ ሆይ
ኃይሉን እንዲሰጥህ ሁሌ ተግተህ ፀልይ
ያን ጊዜ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሆናል
በሣቱም ብትጣል አብሮህ ከዛ ይገኛል
2.
ወደ ዱራ ሜዳ በፍጥነት ወጥታችሁ
ምስል ተዘጋጅቷል በአምልኮ ሰግዳችሁ
ክብር ለባቢሎን ለንጉሱ ስጡ
ብሎ ትዕዛዝ ወጣ ማን ይሆን ቆራጡ
3.
ለእግዚአብሔር የቆሙ ታማኞች ተገኙ
በህዝብ መካከል ሦስት ወጣቶች ታዩ
አምላክ ያድነናል አንሰግድም አሉ
ባያድነን እንኳን እንሞታለን አሉ
4.
የዚህ ዓለም ጥቅም የምድሩ ዝና
በፍፁም ይቅርብኝ አይረባኝምና
ለህያው አምላኬ በውነት እሰግደለሁ
አምላክ ያድነናል ይህንን አምናለሁ
5.
ለሰው ክብር ብለው ሰዎች ሲታዘዙ
ለሚወጣው አዋጅ በፍርሃት ሲገዙ
ክርስቲያን ወገኔ በፅናት ቁምና
አሸንፈህ እለፍ ባምላክ ታመንና