ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #172 / Song #172

አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ
አመልካለሁ ለማንም የማይረታ
አመልካለሁ ግንበኞች የናቁትን
አመልካለሁ የማዕዘን ራስን
1.
የእውቀት ራስ የጠበብ ጌታ
ምንም ቢፈተን የማይረታ
በሰው አእምሮ አይገመትም
ወርዱም ስፋቱም አይዘለቅም
2.
ፈቅሩን አይቼ ቀምሸዋለሁ
ፍጹም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ
ለመከራዬ አርሱ እየገባ
ይጋፈጠዋል ልጄ እያለ
3.
ጥፋቴን ሁሉ በፍቅሩ እያየ
ያሳልፈኛል ልጄ አያለ
ከሁሉም በፊት ፍቅሩ ሰብሮኛል
በመስቀሉ ላይ ነፍሱን ሰጥቶኛል
4.
ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለኝም
እንደርሱ የሚሆን ከቶ አላገኝም
የውስጥ ችግሬን ሳልነግረው ያውቃል
ለኔ ስከብደኝ ይሸከመዋል፡፡
100%
100%