በችግር መከራ አሳድጋ
ምናልባት ልጇን ብትረሳም
እግዚአብሔር ግን ፍፁም አይረሳም x2
አይረሳም x4/ x2
}x2እግዚአብሔር ልጁን አይረሳም
ላፍታም ቢሆን አይዘነጋም
1.
ድንገተኛ አደጋ ድንገት ተከስቶ
ትርምስ ግርግር በሥፍራው በርክቶ
}x2ሁሉም ሲጥር ሊያድን ራሱን
እግዚአብሔር ግን አይረሳም ልጁን
2.
ኤሎሄ ኤሎሄ ብሎ የሱስ ሲጮህ
አምላክ ሆይ አባት ሆይ ሲለው ለምን ተውከኝ
}x2እግዚአብሔር መቼ ልጁን ረሣው
መቃብር ፈንቅሎ አስነሳው
3.
እግዚአብሔር ረስቶናል ትቶናል ምትሉ
ሥፍራችሁን ሳትለቁ ጠብቁት በቃሉ
}x2እግዚአብሔር በጊዜው ይደርሳል
እንባን ከይናችሁ ላይ ያብሣል
4.
ብረሳህ ብተውህ እኔስ ቀኔ ትርሳኝ
አንድም ነገር የለም አንተን የሚያስረሳኝ
ስለዚህ ልጄ አልተውህም
በጭራሽ እኔ አልረሳህም
ስለዚህ ልጄ አልተውሽም
በጭራሽ እኔ አልረሳሽም