አቻምናን በድል አልፈናል
አምናንም ጌታ ረድቶናል
ዛንድሮም እርሱ ስላለን
በጸጋው እናልፈዋለን።
1.
በልኡል መጠጊያ ሚኖር
በአምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል
በሚያልፍ መክራ መሃል
የማያልፍ ታሪክ ይሰራል።
2.
ቁጥራችንን እጅግ ጨመረ
ኃይላችንን አጠነከረ
መከራው አሳልጥኖናል
ሰማያዊ ውበት ሰጥቶናል
3.
ቀናቶች ወራትን ወልደው
ወራትም አመት አራምደው
አልፈዋል ሳይታወቀን
እግዚአብሔር ስለጠበቀን
4.
የየሱስ ስም ተሰበከ
ዲያቢሎስ ተንበረከከ
'ዝማሬ በየአገሩ
የወንጌል ሰፋ ድንበሩ።
5.
ከኢየሩሳሌም ከይሁዳ
በገነት በምድረ በዳ
ይሰማል የደስታ ዜና
ለኢየሱስ ይሁን ምስጋና