ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #33 / Song #33

ጌታ ሆይ ባንተ ሰው ሆኛለሁና

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምስጋና
እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል
ሀዘን ምሬቴንም ከኔ ወስደሃል
1.
ከታላላቆች ካለቆች ጋራ
ፊት ለፊት ቆሜ እኩል ሳወራ
ስለሆንክልኝ ግርማ ሞገሴ
ከፍ በልልኝ ጌታ የሱሴ
2.
አድነኸኛል ከሰቆቃዬ
ባንተ መፅናናት ደርቋል እንባዬ
አቆመኸኛል በተራራ ላይ
አብቅተኸኛል ክብርህን እንዳይ
3.
ባንተ ለምልሞ ምድረ በዳዬ
በረከት ሞልቷል የሕይወት ጓዳዬ
ላይ ታች ከማለት ከሩጫ አርፌ
መብላት ጀመርኩኝ እሸት ቀጥፌ
4.
ዛሬ ጠላቴ ሥፍራውን ለቋል
ከላይ የነበር ከግሬ ሥር ወድቋል
ባንተ ጀግንነት ነፃ ወጣሁኝ
አንተም ስትከብር እኔም ከበርኩኝ
100%
100%