ና በልቤ ተቀመጥ /2/
በውስጤ ያለውን
በደሌን አንሳውና
ንፁህ ሆኜ ልቅረብ ለምስጋና
1.
ወደ አንተ ስቀርብ በፊትህ
አንዳች ነገር የለም የያዝኩልህ
ግን በውስጤ ያለው በኔ የሞላው
መርገም ብቻ ነው ጌታ ሚታየው
2.
ብዙ ጐደሎ አለኝ በህይወቴ
ፍፁምም አይደለም እኔነቴ
መንፈስህን ሁሌ ያሳዝናል
ሥጋዬ ከንቱ ነው ያቆስልሃል
3.
ጌታ ዝም አትበል አትናቀኝ
ጉድለቴን ተመልከት አትተወኝ
ለሌላ ምነግረው ስለሌለኝ
አንተን ጠይቃለሁ ተቀበለኝ
4.
የምትራራ አምላክ መሆንህን
በፊትም አውቃለሁ ማዳንህን
የናዝሬቱ ኢየሱስ አንተ ማረኝ
እለምንሃለሁ ዛሬም አንፃኝ