ኦ ክብር ክብር ክብር ሃሌሉያ
ከይሁዳ ነገድ ለሆነው አንበሳ ለሌለው አምሳያ
ልበል ላመስግነው ከአንጀቴ
ውለታው ስለበዛ የመድኃኒቴ።
1.
ሳላውቀው ያወቀኝ ሳልሻው ያዳነኝ
በአስገራሚ ፍቅሩ እኔን የወደደኝ
ከጥፋት እሩጫ ነፍሴን የመለሳት
ኢየሱስ ነውና ያወጣኝ ከእሳት።
2.
በልጅነት ጊዜ ያኔ በለጋነት
ጠላት ሲጐትተኝ ወይ እዛ ባርነት
ጸጋው ባይበዛልኝ እጁ ባይደግፈኝ
የት ቦታ ነበርኩኝ ክንፉ ባይጋርደኝ።
3.
ጥሩር ሆኖልኛል በጦርነት ጊዜ
ፍለጸ ሲያቆስለኝ በሐዘን ትካዜ
ውለታውን እያሰብኩ ላመስግነው ጌታን
አይገኝምና እንደ እሱ የሚረዳኝ።