ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #35 / Song #35

ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ /2/
1.
እግዚአብሔር ምህረቱ ብዙ
ደካሞችንም ማገዙ
በጀርባው አዝሎ ማሸከሙ
ከኃጢያት ማንፃት በደሙ
2.
እኔስ አይቻለሁ ፍቅሩን
ከፋንድያ ላይ ማንሣቱ
ዛሬ ሰው ሆኜ እዘምራለሁ
ለዚህ ክብር በቅቻለሁ
3.
እጅግ ተንቄ በሰው ዘንድ
ወድቄ ነበር በአመድ
ግን ጌታ ኢየሱስ ፈልጐኝ
ከሀጢያት ማጥ ውስጥ አወጣኝ
4.
አይገርማችሁም ወይ ወገኖች
የልዑል አምላክ ባርያዎች
ተነሱ ዘምሩ ለጌታ
እጅግ ብዙ ነው ውለታው
100%
100%