1.
መንፈሱና ሙሽራይቱ ና ይበሉትና
የሚሰማም ሁሉ ና ይበለውና
የተጠማ ሁሉ ጠጥቶ ይርካና
ማራናታ እንበለው የሱስ ሆይ ቶሎ ና
2.
እነሆ በቶሎ እመጣለሁ ይላል
ለእያንዳንዱ እንደሥራው ዋጋውን ይከፍላል
አልፋና ኦሜጋ አምላክህ እኔ ነኝ
ፊተኛ ኋለኛ መጨረሻ የሌለኝ
3.
የረከሰ ልብሳችን በበጉ ደም ታጥቦ
ሀጢያተኛ ሕይወታችን በየሱስ ተውቦ
ወደ ላይ እንመልከት ጊዜው በጣም ሄዷል
መራናታ እንበለው የመምጫው ቀን ቀርቧል
4.
የሰቆቃ የስቃይ ፅዋው ሞልቷልና
ግፍ መከራ ሀዘን እጅግ በዝቷልና
ይህ ሁሉ የሚያከትመው የሱስ ሲመጣ ነው
ማራናታ የሱስ ቶሎ ና እንበለው