ደመና የለም አዎ ደመና የለም
ነፋስም የለም አዎ ነፋስም የለም
ባዶ ሸለቆ ግን በውሃ ይሞላል
ጠላት አይኑ እያየ ጌታ ያከብረናል
ባዶ ሸለቆ ግን በውሃ ይሞላል
ሰይጣን አይኑ እያየ ጌታ ያከብረናል።
1.
ደመና በሰማይ የለም ነፋስ እንኳ የልም
የምንመካበት ከቶ አልተሰጠንም
የሠራዊት ጌታ እሱ መመኪያችን
ብሩም ወርቁም የሱ ለምን መፍራታችን
ከቶ አንፈራም እኛ ስጋት አይገባንም
ይሞለዋል የሱስ አያሳፍረንም
2.
ደረቅ ምድረ በዳ ነፋስ የሌለበት
የጠራ ሰማይ ነው ጉም የማይታይበት
በሠራዊት ጌታ ተማምነንበታል
ባዶ ሸለቆአችን ሞልቶ ሞልቶ ይፈሳል
ምንም ምንም ባይኖር የሞያዝ የሚጨበጥ
አንዱ የሱስ ካለ ይመጣል ካለበት።
3.
በምንም በማንም አንተማመንም
ኢየሱስ ይበቃል ሌላ አንፈልግም
እሱ ከዙፋኑ ከተንቀሳቀሰ
ጎበዝ ምን ይመጣል ከየሱስ የባሰ
ሁሉ በሁሉ ነው ይህ ድንቅ ጌታ
ታሪክን ገልብጦ ያቆማል በከፍታ
4.
ሁሉ በእርሱ ይሆናል ሁሉ በአምላካችን
የለእርሱ የሚሆን ይጥፋ ከዙሪያችን
በሰው አንመካም የከንቱ ከንቱ ነው
የናዝሬቱ ኢየሱስ ካለልን በቂ ነው
በሱ ተመክተን እንዴት እናፍራለን
ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።