ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #144d / Song #144d

ተመስገን ነው

English translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ተመስገን ነው ተመስገን ነው
ምን አለ ጌታችን?
በአንተ ያላለፍነው?
በአንተ ያላሸነፍነው?
1.
ዳገቱን ወጣነው አንተ እየመራኸን
ቁልቁለቱን ወረድን አንተን ተከትለን
ይኸ ሁሉ ሲሆን አንዴም አልተረታን
በድል ስላለፍን እንበልህ ተመስገን
2.
አታውቁም ተባልን ስምህን ስለያዝን
እንደ ሞኝ ተቆጠርን በእኛ ስላለህ
ይሁን አይከፋንም እጅግ ደስ ይለናል
ጌታችን ስትመጣ ሁሉም ይገለጻል
3.
ነፋስ ነፈሰበት በኩራዛችን ላይ
ለማጥፋት እንዳይነድ ለሁሉም እንዳይታይ
ግን ሥራህ ድንቅ ነው ቦግ ብሎ በራ
በርቀት ያሉትን ወደ አንተ እየጠራ
4.
የመልካም ሁሉ ምንጭ አንተ ነህ ጌታችን
ቁጣህን መልሰህ በፍቅርህ ያቆምከን
ያ ሁሉ ውለታህ ጌታ ትዝ ሲለን
ደግመን ደጋግመን ኢየሱስ ተመስገን
100%
100%