1.
ገና ተጓዥ ነኝ የሩቅ አገር ሰው
በጌታዬ ቤት ስደርስ ነው የማርፈው
በጉን በግርማ ፊት ለፊት ሳየው
በዚያ እኖራለሁ ሆኜ አዲስ ሰው
እስከዚያች ቀን ግን በጣም እተጋለሁ
መከራም ቢሆን በሥሙ አልፋለሁ
ሃሌሉያ ምን ይሳንሃል አሜን
ሃሌሉያ ሁሉ ችለሃል
ሃሌሉያ ዮርዳኖስም አሜን
ሃሌሉያ ክንድህ ከፈለው
ማዕበሉን ደግሞ ቃልህ አዘዘው
2.
ብደክም ብዝል ብወድቅ ብነሳም
ስማቅቅ ብኖር ከእርሱ አልለይም
የአሁን ክሳቴ ጉስቁልናዬ
ሁሉም አይኖርም ሳገኝ ጌታዬን
አንድ ቀን ከጽዮን ድምጹን ስሰማ
እበረታለሁ ሁሉም ያልፍና
3.
ትላንት ተዋግቶ ነፍሴን ካዳናት
ዛሬ የሚታክት አምላክ መች አላት
አይለወጥም ዛሬም ኃያል ነው
በእውነት አምላኬ የድል ጌታ ነው
ስለዚህ ጠላት ተስፋህ ይደምሰስ
ነው መሠረቴ ዓለቴ የማይፈርስ