1.
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ኃያል ጌታችን
በየጧቱ ላንተ እንዘምራለን
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
መኃሪና ኃያል
እግዚአብሔር
የዘለዓለም ገዥ
2.
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
መላእክት ያክብሩህ
ዘውዳቸውን በዙፋንህ
ዙሪያ ትተው
አዕላፋት በሰማይ
ይሰግዱልሃል
አምላክ የነበርህ
ያለህ የምትኖር
3.
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ክብርህ ቢጋረድ
ግርማህን የሰው ዓይን
ሊያየው ባይችል እንኳ
ብሩክ አምላክ ቅዱስ ነህ
እንዳንት አይገኝም
የተሞላህ በኃይል በፍቅር