1.
ከጠላት ፍለጻ ከሰይፍ ያድንሃል
በረሃብም ዘመን ከሞት ያስጥልሃል
ስሙን ያስከብራል ቁም ነገርን ያውቃል
ሕጻን ስላይደለ ያለውን ይፈጽማል ።
ኢየሱስን እንደ ሰው አትጠራጠረው
መዋሸት አያውቅም ተስፋህን ጠብቀው
አይጥልህምና በመከራ ጥራው
አፍህ እያመነው በልብህ አትክዳው።
2.
ለታማኝነቱ ተው ገደብ አትስጠው
ለወላዋይ ልብህ ጽናት አትንፈገው
የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር አይዋሽም
የገባልህን ቃል ፈጽሞ አይክድም።
3.
ከእርሱ ጋር ከሆንክ ከአንተ ጋራ ነው
አውጥቶ እንዳይጥልህ ብቻ አትተወው
አስብ ቆም ብለህ ያለፍከውን ዘመን
ዛሬም አምነህ ጥራው ያኔ ያዳነህን።
4.
ስሙን እየጠራህ ስንቱን አምልጠሃል
ከስንቱስ አደጋ ስንት ጊዜ ድነሃል
ውለታውን ሲረሱ ጌታ ቅር ይለዋል
በቃሉ ብታምን ሁሉ ይቻልሐል።