በችግር ቀን የሚረዳ
}x2ካንተ ሌላ አላገኝም
ብዞር ብዞር በዚህ አለም
1.
ወዳጄ የሱስ መልካም እረኛ
ሚስጥረኛዬ የልብ ጓደኛ
መመኪያዬ ነህ ጥላ መከታ
የነፍሴ ጥማት የልቤ እርካታ 2X
2.
ወዳጄ ያልኩት ሚስጥር ሚካፈል
ለችግር ጊዜ ከጐኔ የሚሆን
}x2ሲሄድ ኮብልሎ ዋሽቶ ቢከዳኝ
የሱስ አንተ ነህ ወዳጅ የሆንከኝ
3.
ያኔ በምቾች ዙሪያዬን ከበው
ከእጄ በልተው ከእጄ ጠጥተው
}x2በስንት ቁልምጫ ሲክቡኝ ኖረው
ከጐኔ ጠፉ ወዳጅ ያልኳቸው
4.
ሀብቴ ተሟጦ ባዶ እጄን ብቀር
ሁሉም ሲርቀኝ በጣም ብቸገር
}x2ቀርቦ የሚያፅናናኝ ወዳጅ ሲጠፋ
የሱሴ አንተ ነህ የሆንከኝ ተስፋ
5.
ጊዜ የማይሽረው ፍቅሩ የማያልቅ
ይቅርታው ብዙ ወረት የማያውቅ
}x2ለወዳጅ ታማኝ ቃሉ እውነተኛ
የለም እንዳንተ የልብ ጓደኛ