ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #70 / Song #70

ሁሉም በአገልግሎቱ ይትጋ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
በሠማይ አለውና ዋጋ
1.
ጌታ በቤቱ ያቆመህ
ላገልግሎቱ የመረጠህ
በቃሉ ነብሳትን ማራኪ
በርታ ፅና /2/ አንተ ሰባኪ /2/
2.
በቤቱ ጳጳስ ያደረገህ
ለመንጋውም መሪ የሆንህ
በቤቱ የምትቆም ሁሌ
ተጠንቀቅ /2/ አንተ ሽማግሌ /2/
3.
ቃሉን ለህዝቡ እንድትናገር
ፈውስንም ደግሞ እንድትመሰክር
በቤቱ ያቆመህ ተናጋሪ
ቸል አትበል /2/ አንተ አስተማሪ /2/
4.
ታላቅነቱንም መስካሪ
ሀያልነቱን ተናጋሪ
ሥራውን በዜማው አዋሪ
በስጦታህ /2/ በርታ ዘማሪ /2/
5.
ጌታችን በቤቱ ያቆመን
በርሱ የታመን ሁላችን
ባገልግሎታችን እንትጋ
በርሱ ዘንድ /2/ አለህና ዋጋ /2/
100%
100%