ስላደረክልን እናቅርብ ምሥጋና (2)
ምህረትህ ለልጅ ልጅ ጌታ ሆይ አላለቅምና
1.
አንመሰክራለን ታማኝ ነህ ጌታችን
ውለታ አድርገሃል ለቤተሰባችን
እኛም እንዳናፍር ስምህን አከብረሃል
u>ታማኝ (2) መሆንህን ጌታ መስክረሃል
2.
በቃልህ ተስፋ ላይ ልክ እንደተጻፈው
የልባችንን መሻት በሙሉ ፈጸምከው
ከአርያም ደርሶ የለመንንህ ሁሉ
ለእኛ (2) ስላደረከው ሰዎች ዕልል አሉ
3.
እንወድስሃለን በቅኔና በመዝሙር
ስለገለጽክልን ሰማያዊ ፍቅር
ስለዚህ ጌታ ሆይ በሰዎች ፊት ቆምን
ላንተ ለስምህ ምስጋና እንዘምራለን
4.
እንመሰክራለን አናፍርም ሁልጊዜ
አውጥተኸናልና ከመንፈስ ትካዜ
በለቅሶአችን ፈንታ ሰጥተኸናል ደስታ
ክብር (2) ይሁን ለአንተ የሠራዊት ጌታ