እኛ አባት አለን 2x
በጌታ በኢየሱስ ላይ ተማምነን
ይህን ጠፊ አለም እናልፋለን
1.
ከህፃንነታችን በድንቅ አመራርህ
እየመራህ ዛሬ አቆምከን ለክብርህ
በኑሮአችን ዘመን ያለውን ማዕበል
ጸጥ እንዲል አዘዝከው ታላቁ እግ/ር
2.
በዘርና ጐሣ ሊከፋፍል ሰይጣን
ቆርጦ ተነሣና ከምድር ሊያጠፋን
አቤት ምህረትህ መች ያልቅብህና
እንዳንጠፋ አስበህ ከተትከን በጐያህ
3.
ጥንትም ለነበርከው ዛሬም ለምናይህ
አቤቱ አይለየን ታምረኛው ክንድህ
አለማመናችን ጌታ እርዳንና
በጸጋህ አቁመን ዛሬም እንደገና
4.
ክብሩ የሚያስፈራ ግርማ ሞገስ ያለው
በሠማይ ሠማያት ተፈርቶ ሚኖረው
መልአክ ቀንና ሌት ወድቀው ሚሠግዱለት
የነገሥታት ንጉሥ አለን እኛስ አባት