መንበርከክ መፀለይ ካለ
ሁሉም ነገር በእጃችን አለ
1.
ሙሴ በኮሬብ ተራራ እግ/ርን ያናገረው
በደመና ውስጥ ተከቦ ክብሩን ማየት የቻለው
አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመጾም በመፀለይ ነው
2.
ሀና ለረዥም ዓመታት በምላስ ዱላ ተመታ
ጣውንቷ ስታስጨንቃት ሁልጊዜ ጠዋትና ማታ
ለአምላኳ ነግራ አልቅሳ ሳሙኤልን ሰጣት ጌታ
3.
ኤልያስ ሦስት ዓመት ሙሉ ዝናብ እንዳይወርድ የዘጋው
በፆም በፀሎት ሀይል ነው አመፀኛውን ህዝብ የገዛው
ለነገሥታትና ለአህዛብ ያአምላኩን ክንድ የገለፀው
4.
ባንበሳ ጉድጓድ ውስጥ አድሮ ዳሪዮስ ጠርቶ የጠየቀው
ዳንኤል አሳደረህ ወይ አምላክህ የምታመልከው
አዎን ድኜ አድሬአለሁ አምላኬን አከብረዋለሁ