በኔ የተጀመረው እግዚአብሔር ስራ
የሚቆም አይደለም በተልካሻ ስፍራ
የጀመረው እግዚአብሔር ታማኝ
1.
በኔ የተጀመረው እግዚአብሔር ስራ
የሚቆም አይደለም በተልካሻ ስፍራ
እኔም ወጥቻለሁ ልሄድ ልራመድ
በሚሆን በማይሆን ላልቆም በመንገድ
2.
ከፊቴ የቆሙ እንቅፋቶች ሁሉ
መራመድ ስጀምር ይነቃቀላሉ
ስለዚህ በምንም ልቤ አይሸበርም
አንደ ንስር በክንፍ መብረሬ አይቀርም
3.
አቀበት ቁልቁለት ከፍታ ዝቅታ
ከቶ አያቆምኝም ከመሄድ ለአንዳአፍታ
ውስጤ ያለው ቅባት የሚያሸንፍ እንጂ
ሚሸነፍ አይደለም በጠላቶች እጅ
4.
ሺ ጊዜ ቢበዛ የጠላቶች ጉልበት
ጥሼው እወጣለሁ በየሱሴ ብርታት
ቅባቱን የሰጠኝ የታመነው ጌታ
ያስኬደኛል አዎ በጠላት ከፍታ