1.
በእረኛቸው የታመኑ በየመስኩ የትስማሩ
ዱካውን እየተከተሉ ለደህንነት የተጠሩ
ከጨካኝ አውሬ የዳኑ ከመታረድ የተረፉ
ሐሴትን እንደሚያደርጉ በአጥፊው ጥፋት ስላልጠፉ።
አዲስ ዝማሬ እንዘምር
ለመድኃኒታችን ክብር
የምሥጋናችንን ሽታ
እናሳርግ በእልልታ
2.
ማቃችንን ቀዶአልና ጸጋውን አልብሶናልና
ክብራችን ትዘምርለት ፍቅሩ አጽናንቶናልና
ጉዳታችንን የሚሹ ጉድጓድ ምሰው የጠበቁን
እጋንንት አፍረዋልና ያደፈጡ ሊያጠቁን።
3.
በፍጹም ልብ እንዘምር በአምላካችን ደስ ይበለን
እናጨብጭብ እልል እንበል ለምንስ እንቆጥባለን
በምሥጋናችን ዝማሬ ምሽጉን እናፈርሳለን
በመንፈሣዊ ጦር ዕቃ ድል በድል እንሄዳለን።