ብርቱ የሆነው አለት ወገኖች የጠሉት
መላው አለም ሸክሙን ቢያሳርፍበትም
ሁሉን ይቋቋማል ቅንጣት አይከብደውም
1.
ሩህሩህ ነው አምላኬ ሆደ ቡቡ /2/
ከጥፋት የሚያድን እርሱ ነው መርከቡ
ኤልሻዳይ ነው ኢየሱስ ክንደ ብርቱ /2/
ለፍጥረታት ሁሉ አቤት ምህረቱ /4/
ግሩም ነው ድንቅ ነው /2/ ውበት ደም ግባቱ
2.
ለፍጥረታት ሁሉ ልዩ ፍቅር ያለው
ኤልሻዳይ የሱስ ሆደ ቡቡ ነው
ዛሬ ተሽቀዳድመው ከእግሩ ሥር የሚያርፉ
ዕረፍት ያገኛሉ ከቶ አንዳች ሳይለፉ
3.
አልፋና ኦሜጋ የሆነው ኢየሱስ
ዘላለማዊ ነው የማይሻር ንጉስ
አርነት ያወጣን የነፍሳችን ቤዛ
ግሩም ድንቅ አምላክ ነው ሁሉን የሚገዛ
4.
ከነገድ ይሁዳ የሆነው አንበሳ
በዲያብሎስ ሠፈር በብርታት አገሳ
በታላቅ ስልጣኑ ማኀተሙን የፈታ
ክብር ይገባዋል የድሆች አለኝታ