የሚሰማኝ ቢኖር የሚያዳምጥ ድምፄን
ወደርሱ ገባለሁ እራትም እበላለሁ
የልብ ጓደኛ ሚስጢረኛ ሆናለሁ
1.
ሰላምና ደስታ ለሚፈልግ እፎይታ
እሆንለታለሁ የዘላለም እርካታ
ኃጢያትና ሌላን ሁሉ አነፃለሁ
ማደሪያዬንም በዚያ አደርጋለሁ
2.
እንደጳውሎስ ላለው እኔን ለሚያሳድድ
አሳየዋለሁኝ የህይወትን መንገድ
የከፈተ በሩን ሆኖ ፈቃደኛ
ረዳት ያገኛል የልብን ጓደኛ
3.
ድምፄን የሚያዳምጥ የሚሰማኝ
ቢኖር እገልጥለታለሁ የሰማዩን ሚስጢር
ህዝቤ ሆይ አትሞኝ ክፈትልኝ በሩን
እሰጥህማለሁ ሁሉን የምትሻውን
4.
ድምፄን የሚያዳምጥ የሚሰማኝ ቢኖር
እገልጥለታለሁ የሰማዩን ሚስጢር
ህዝቤ ሆይ አትሞኝ ክፈትልኝ በሩን
እሰጥህማለሁ ሁሉን የምትሻውን