አይደለም የእኛ አምላክ ሞት የሚያሸንፈው
በመስቀል ቢሞትም ድል አርጐ ተነስቷል
ዛሬም ለዘላለም ሞትን ድል ነስቶታል
1.
ሀሌሉያ ደስ ይበለን ጌታ ኢየሱስ ከሞት ፈታን
ሀሌሉያ ደስ ይበለን አምላካችን ክበርልን
2.
በጥፊ ቢመታም ደግሞም ቢተፋበት
በመስቀል እንዲሞት ሞት ቢፈረድበት
ስቃይ ሞት መከራ በመስቀል ታግሶ
ከሞት ሰንሰለት ውስጥ አወጣን በጣጥሶ
3.
ደዌአችንን ሁሉ እርሱ ተሸከመ
በመስቀል ላይ ሞተ ደቀቀ ቆሰለ
እዳችንን ሁሉ ጌታ ከፈለልን
የዘላለም ሕይወት በደሙ አገኘን
4.
ከጌታ-ሰማኔ እንደ ወንበዴ ይዘን
ጐልጐታን ተራራ መስቀል አሸክመን
በሚስማር ቸንክረን ብንሰቅለውም እንኳን
ስለኛ ፀለየ ይቅር እንድንባል