ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #73 / Song #73

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የኔ ጌታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ሽንፈትን የማታውቅ ከቶ ፍፁም ማትረታ
አልፋና ኦሜጋ የሕይወት እርካታ
ነፍሴ ናፍቃለች ናልኝ ማራናታ /2/
1.
ከፋርኦን ጮማ ቤት ስደት ይሻለኛል
ከሕዝብ ጋር ሆኜ መኖር ያዋጣኛል
ከነገስታት ሁሉ ትበልጣለህና
አንተን መርጫለሁ የሱስ ሆይ ቶሎ ና /2/
2.
ከጨለማ አውጥተህ ብርሃን ሰጠኸኝ
ቀይ ባሕርን እንዳልፈው ረዳት የሆንከኝ
በዘመኔ ሁሉ ባርኮት ያስቆጠርከኝ
ለሰማይ መንግሥትም ገጣሚ አድርገኝ /2/
3.
አንተን ጠርቶ ደግሞ ያፈረ ሰው ማነው
ሁሉን ታከብራለህ ፍቅርህ ወሰን የለው
ለተማመነብህ ነፃ ታወጣለህ
የጽድቅንም ሕይወትም ታጐናጽፋለህ /2/
4.
በጌታ ቤት መኖር ታላቅ ዋጋ አለው
በስሙ መጠራት ልዩ በረከት ነው
ለጊዜያዊ ጥቅም ከሚገኘው ደስታ
የሱስ ይሻለኛል የሕይወት እርካታ /2/
100%
100%