ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #278d / Song #278d

ወደ አንተ መጥተናል ጌታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ወደ አንተ መጥተናል ጌታ
ወደ አንተ መጥተናል
በዓለም ዞረናል ኢየሱስ ሁሉንም አይተናል
ዕርካታን ለማግኘት ስንል ተንከራተናል
ይቅር በለን ተቀበለን እባክህን አንተን በድለናል
1.
ጉስቁልናን ተሞልተናል እጅግም ረክሰናል
ታላቁን መዳን በመናቅ መከራ ጠግበናል
ውኃ አልባ ጉድጓዶችን ለራሣችን ቆፍረናል
ከሕይወት ውኃ ምንጭ ርቀን በጥማት ደርቀናል
2.
የዚህ ዓለም ጉስቁልና ሰልችቶን መርሮናል
አቅጣጫ ቀይረን ከጥፋታችን መጥተናል
ሰማይና ምድር በኢየሱስ ደም ታርቀዋል
የጥልም ግድግዳ ደግሞ መፍረሱን ሰምተናል
3.
ለማይረባ ነገር ብለን ክብራችንን ለወጥን
ለጥፋት ምሣሌ መተረቻ መዘባበቻ ሆንን
ግን እጅህን ዘርግተህ ወዳንተ መራኸን
መጋረጃን ቀደህ ወደ መቅደስህ ጋበዝኸን
እንደ ጥፋታችን ከቶ አልመለስክብንም
ዕድፈታችንንም አይተህ አልተጸየፍከንም
በደምህ አጥበኸን ዛሬ ሕይወት እንሸታለን
ስለ ምሕረትህ ምሥጋና በደስታ ዕልል እንላለን
280
4.
የዕውቀት ራስ የጥበብ ጌታ
ምንም ቢፈተን የማይረታ
በሰው አእምሮ አይገመትም
ወርዱም ስፋቱም አይዘልቅም
አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ
አመልካለሁ በማንም የማይረታ
አመልካለሁ ግንበኞች የናቁትን
አመልካለሁ የማዕዘን ዕራስን
5.
ፍቅሩን አይቼ ቀምሸዋለሁ
ፍጹም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ
በመከራዬ እርሱ እየገባ
ይጋፈጠዋል እንዳልረታ
6.
ጥፋቴን ሁሉ በፍቅር እያየ
ያሳልፈኛል ልጄ እያለ
ከሁሉም በፊት ፍቅሩ ሰብሮኛል
በመስቀሉ ላይ ነፍሱን ሰጥቶኛል
7.
ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለኝም
እንደርሱ የሚሆን ከቶ አላገኝም
የውስጥ ችግሬን ሳልነግረው ያውቃል
ለእኔ ሲከብደኝ ይሸከመዋል
100%
100%