ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #318d / Song #318d

አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሀለሁ /2X/

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሀለሁ /2X/
1.
ጎሊያድን መሳይ አስፈሪ ጀግና፣
ግዙፍ ሰውነት ግሩም ቁመና፣
ራሱን ተመቶ የተዘረረው፣
በኔ ሃይል አይደለም ባንተ ጉልበት ነው፣
ሌላ ምን አለ ሃሌሉያ ነው።
2.
ሳኦል በክፋት ጦሩን ሲሰብቅ፣
ከግርግዳ ጋር ነፍሴን ሊያጣብቅ፣
ቢወረውርም ደግሞ ደጋግሞ፣
ጋሻ ሆነልኝ ያንት እጅ ቀድሞ፣
አቤት ማዳንህ ይግነን ዙፋንህ።
3.
ከውስጥ ከውጭም ከቅርብም ከሩቅ፣
ተሰድጃለሁ ምክኛቱን ሳላውቅ፣
የማምለጫ አለት ምሽግ የሆከኝ፣
አንተ ነህ ጌታ የሰበሰብከኝ፣
ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ።
4.
በጨለማ ውስጥ በሞትም ጥላ፣
በጥፋት ጉርጓድ በሌለው መላ፣
ባለቀ ሰአት ደርሰህልኛል፣
የናሱን ደጃፍ ሰብረህልኛል፣
ታላቅ ነው ሀይልህ ከፍ ይበል ስምህ።
100%
100%