ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #65 / Song #65

ይመስገን ጌታ አሜን ይመስገን የሱስ /2/

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ለዚህ ያበቃን ገናናው ንጉስ
1.
ትላንትን አልፈን ዛሬ ደርሰናል
የነገውንም ጌታ ያሳካል
ፍፁም ሰላምን ከሱ አገኘን
በፍቅር አይቶ ጌታ ባረከን
2.
በበደላችን ከቶ ላይተውን
በቃል ኪዳኑ ፀንቶ ጠበቀን
እንደሥራችን ከቶ ሳያየን
የመስቀል ፍቅሩ ሰው አደረገን
3.
ነውራችንን ጌታ ለወጠው
ባዶነታችን በመንፈስ ሞላው
ለአገልግሎትም ዛሬ መረጠን
ለሰማይ ሥፍራ እኛንም አጨን
4.
ስማችን ጠፍቶ ወድቀን ነበረ
ነገር ግን ጌታ ዛሬ ከበረ
ለየሱስ ታዲያ ምንስ ይሰጠው
ከፍ ይበል ጌታ ምስጋና ይድረሰው
100%
100%