በመከራም ቢሆን በፈተና
በአንተ ብቻ ልቁም ልትጋና
ፍፃሜዬን አሳምር ድል ስጠኝና
1.
ወገቤ ላልቶ እምነቴ ደክሞ
ጐልበቴ ዝሎ መንገዱም ረዝሞ
የያዝኩትን ለቅቄ በከንቱ ቦታ
በሜዳ እንዳልቀር ጠብቀኝ ጌታ
2.
ከፊት ለፊቴ ያለኝን ተስፋ
በርቶ የሚኖረውን ከቶ የማይጠፋ
በድል ነሽ እጆቼ እስክጨብጠው
አደራ ጌታ ሆይ ጐልበቴን አፅናው
3.
ከሁሉም የሚበልጠውን የሰማዩን ሚስጥር
አንዴ አይቻለሁ ሁሉም ነገር ይቅር
በትዕግሥት በእምነት ሩጫዬን ፈፅሜ
አክሊል እንድሸለም እርደኝ መድህኔ
4.
ባየሁ በሰማሁ ዘውትር ፀንቼ
በተረዳሁ እውነት እንድቆም ተግቼ
ወለም ዘለም ሳልል ሳላመነታ
ከግቡ እንድደርስ እጄን ያዘኝ ጌታ
5.
ፈተና ቢበዛም በእምነት ጐዳና
መከራም ቢበዛ ጐልበቴን አፅና
በታማኝነት አንተን አስከብሬ
እንድገኝ እርዳኝ በሰማይ አገሬ