ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #19h / Song #19h

ባርኮትህን ቁጠር

Count Your Blessings

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
በሕይወት ማዕበል
ጐርፍ ስትንቀጠቀጥ
ሁሉም ጠፍቶብህ
ተስፋህም ሲቆረጥ
ባርኮትህን ቁጠር
ዘርዝር በተራ
ወዲያው ታስባለህ
ያምላክን ሥራ
ባርኮትህን ዘርዝር በተራ
አይተህ ተገንዘብ የርሱን ሥራ
ባርኮትህን ዘርዝር በተራ
አይተህ ተገንዘበው
ያምላክን ሥራ
2.
በከባድ ሸክም ኃይል
ተጭነሃል ወይ? የጥሪውስ መስቀል
ከበደብህ ወይ?
ባርኮትህን ቁጠር
ጥርጥር ይብረር
በዘመንህ ሁሉ
በደስታ ዘምር
3.
ወደ ሌሎችም
ሀብት ስትመለከት
አስብ የክርስቶስን
ባለጸግነት
ባርኮትህን ቁጠር
አይገዛውም ሀብት
ያንተንም ነፍስ ዋጋ
በሰማዩ ቤት
4.
ትልቅም ቢሆን
ትንሽ ጭንቅ መከራ
ተስፋ ሳትቆርጥ
አምላክህን ጥራ
ባርኮትህን ቁጠር
መላእክት ይስሙት
ለጉዞህም ብርታት
ይስጡህ መጽናናት
100%
100%