1.
በሰማይ መዝሙር ሲዘመር
ሰምተነው የማናውቀው
መላዕክት ሲያመሰግኑት
በዙፋን ላይ ያለውን
በተቃኘ በገናቸው
ባማረውም ድምፃቸው
ኦ እኛም ጌታ የሱስን
ከልብ እናገልግለው
ቅዱስ ቅዱስ ብለው ሲዘምሩ
እኔም ተባብሪያቸው
የሰማይን ቤት ላደምቅ
ግን የመዳን ታሪክ
ስዘምር ያዳምጣሉ
መላክት ከቶ አላወቁም
የመዳንን ደስታ
2.
ግን ሌላ መዝሙርን ሰማሁ
አስደሳች በሆነ ድምፅ
እኛን ላዳነን ለጌታ
ለገዛን ነው መዝሙሩ
መከራን ሁሉ ያለፍን
ወደዚያች ግሩም አገር
በሚወርደውም ንፁህ
ምንጭ ልብሳችንን አነፃው
3.
መላዕክት ቆመው ሲሰሙ
ያልዘመሩትን መዝሙር
እነዚያ በደም የነፁት
በብዙ ፏፏቴ ድምፅ
ስለመከራ ዘመሩ
ድል የነሱትን ውግያም
ታላቁን አዳኝ ወደሱት ያመሰገናቸውን
4.
እኔ ምንም መልአክ ባልሆን
ከዚያ ያለውን አውቃለሁ
አዝማቼን እዘምራለሁ
መላክት ያልዘመሩትን
ላዳኜ እዘምራለሁ በጨለማው መስቀል ላይ
በደሌን ለደመሰሰው
ከኃጢአቴም ላነፃኝ