ክበር ስምህን እጠራለሁ
ጌታ ሆይ /2/ ዛሬም በፊትህ እጮሃለሁ
እባክህ ማረኝ እላለሁ
1.
ማንም አላፈረም ስምህን የጠራ
ኑሮው አስጨናቂ ቢሆን ፍፃሜ ታላቅ ነው
ጅማሬ ታናሽ ቢሆን ፍፃሜ ታላቅ ነው
ኤልሻዳዩ ጌታ ሁሌ ከእኔ ጋር ነው
--- ዳን. 6፤19-22
2.
በቀን ሦስት ጊዜ መፀለዬን ሰምቶ
የጠላቴ ቁጣ በእኔ ላይ በርትቶ
በአናብስት ጐድጓድ እንድጣል ቢተጋ
የማመልከው አምላክ የአንበሳን አፍ ዘጋ
--- ዳን. 6፤23
3.
እኔን በከሰሱት በጠላቴ ጭፍሮች
የንጉሱን ቁጣ በእነርሱ ላይ ፀናች
በአናብስት ጐድጓድ ሰብስበው ጣሉአቸው
አንበሶች ያዙአቸው ሁሉን ሰበሩአቸው
--- ዳን. 6፤24
4.
ንጉሡም አዘዘ በምድር ለሚኖሩ
ልዩ ልዩ ቋንቋ ወደሚናገሩ
የማመልከውን አምላክ በፊቱ እንዲጠሩ
አዝዣለሁ አለ ጌታን አከበሩ
--- ዳን. 6፤25-27