ከኔው ነው ችግሩ ጌታ ሆይ ማረኝ
ማድረግ የሚገባኝን አለማድረጌ ነው
መሥራት የሚገባኝን አለመሥራቴ ነው ምፃትህን ያዘገየው
1.
ብዙ ጊዜ በምድር ላይ በስቃይ እንድቆይ
ፈቃድህ አይደለም እንድጨነቅ በዓለም ላይ
አላፊውን ነገር ተስፋ አርጌ ማየቴ ነው
በአፍ ብቻ መራናታ ቶሎ ና ማለቴ ነው
2.
አንተ የሰጠኸኝን ትዕዛዝ እምቢ ብዬ
ለመዳን ማይረዱኝን ጣኦቶች ተከትዬ
በዚህ በእርግማን አለም የኖርኩት ደክሜ
የእኔው ነውና ምክንያቱ ግልፅ ነው መጐዳቴ
3.
ካለማወቄ የተነሣ ለምንድነው የዘገየህ
ቶሎ ና ለምን ቆየህ ይህንን እያየህ
በማለት ምንም ሳይኖር ከልብ የሆነ ዝግጅት
አስጨነቅሁህ ጥፋቱ ከእኔው መሆኑን በመርሳት
4.
ለነፍሣት ውድቀት ምክንያት የሆንኩኝ እኔው ነኝ
ላለመምጣትህ ምክንያት የሆንኩኝ እኔው ነኝ
ብዙዎች በቤትህ ጸንተው እንዲኖሩ ነግሬ
አንተ አስበኝ እንጂ ወዴት ነው ያለሁ ዛሬ