ለእውነት ሲሉ እንደተሰው ጀግኖች
እኛም ጌታ በዘመናችን
እንሻለን ስጠን ያን ፅናትን /2/
1.
የማይደክም ጉልበት ስጠን
የማይዝል በኃይል የተሞላውን
እንደዐለት የፀናውን እምነት
አምላክ ሆይ ስጠን ከመለኮት
2.
የሰማይን የእውነት ኃይል ታጥቆ
የጨለማን ሠራዊት ዘልቆ
እስከፅዮን የሚያደርሰውን
ጌታ ሆይ ብርታትህን ስጠን /2/
3.
ተስፋችን አንተነህ አቤቱ
ሀይልህን ስጠን አሁን ነው ሰዓቱ
የተሰጠን የሰማይን እውነት
እንድናውጅ አፋችንን ክፈት /2/
4.
እንደዐለት የፀናውን እምነት
ለአላማው ቆራጥ ሀይማኖት
እንሻለን የመንፈስን ድፍረት
ጌታ ስጠን የማይደክመውን ጉልበት /2/