ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #90d / Song #90d

አድርገህልኛልና

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 6
1.
ካንተ የተነሣ በሆነልኝ ነገር
ከማመስገን በቀር እኔ ምን ልናገር
አስበህ አቅደህ በሰጠኸኝ በሙሉ
ጌታ ስምህ ይክበር አመሰግንሃለሁ
ከእኔ የሆነ የለም አንድም አልለፋሁም
እንዲያው ሰጥተኸኛል ይህን አልረሳሁም
ስለዚህ ጌታዬ ለኔ ስላሰብከው
ተረድቼአለሁ ስምህን ላክብረው
አድርገህልኛል ከአዕምሮዬ በላይ
ጌታዬ ተባረክ በምድርም በሰማይ(3)
አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ። (3) 2
2.
ዕድሜዬን በሙሉ ብለፋና ብጥር
የማላገኘውን ሰማያዊ ምስጢር
ለልቤ ተናግረህ ልቤንም ባረከው
ከዚህ ሁሉ በላይ የራስህ አረክው
አምላኬ ጌታዬ ምርጫዬ አደረክህ
አንተ ከመረጥከኝ ወዴት እሄዳለሁ
ካንተ የበለጠ ምንስ እገኛለሁ
ለአንተ ለአምላኬ ሁሌ እገዛለሁኝ። (3)
3.
ነፍሴንም ባረካት ሥጋዬን ፈወስከው
ባርኮትህን ሁሉ በቤትህ አፈሰስከው
ወደ አንተ መጥቼ ምንም አልጎደለኝ
ነፍስና ሥጋዬን በሙሉ ባረክልኝ
አለሁኝ በቤትህ ገናም እኖራለሁ
እንደምታቆመኝ እታመንሃለሁ
ንጉሤ ከሆንህ ቤቴን የምትገዛው
ይህ ነው መሻቴ የለኝም ከዚህ ሌላ
ጌታዬና አምላኬ በሕይወቴ ላክብርህ
ይሄ ነው ምኞቴ ዘመኔን ልሰጥህ (2)
ይሄ ነው ምኞቴ ዕድሜዬ ልሰጥህ (2)
100%
100%