1.
ምስኪን ሲጮህ በጨለማ
ወይ የሚል አጥቶ የሚሰማ
ትንፋሽ አጥቶ ጣር ሲይዘው
ትደርሳለህ ልትረዳው
ኢየሱስ የሳሮን ጽጌረዳ
የውስጥ የልብን የምትረዳ
የተሰወረን ትገልጣለህ
መዝሙር በሌሊት ትሰጣለህ
ከጌጥም በላይ ጌጥ ነህ
ከወርቅ ከእንቁ ትበልጣለህ (3)
2.
ክፉው አይሎ እጅ እግር ሲያስር
ሲያሰናዳ ለመቃብር
የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ
ሞትን የሚጥል ቃልም አለህ (3)
3.
ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው
ለተጐዳው ለቆሰለው
ውስጥ አዋቂ የልብ ወዳጅ
ለሁልጊዜ የምትመች (3)
4.
ከጥላህ ሥር ለሚኖሩ
ባንተ ፍቅር ለታሰሩ
ለጉሮሮ ፍሬ ጣፋጭ
መዓዛሀ መልካም የማትስለች (3)
5.
ደናግሎች አንተን ወይው
ተከተሉህ ሁሉን ትተው
ስላወቁ ማጽናናትህን
ከወርቅ ከዕንቁ መብለጥህን (3)