ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #302d / Song #302d

ይህን ኢየሱሴን ምን ላድርገው

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ይህን ኢየሱሴን ምን ላድርገው
ማን ልበለው ምኔን ልስጠው
ክበር እንዳልላው ከብሯል
ንገስ እንሳልነው ነገሷል
ልስጥህ እንዳልለው ሁሉም ነገር አለው
ምድርና ሞለዋን የያዘ ጌታ ነው
ታዲያ ኢየሱሴን ምን ላድርገው።
1.
በኔ ኃጢአት ምክንያት የመስቃል ላይ ጣሩ
ገላውን የበሳው ጦርና ሚስማሩ
ዛሬም ጠዋት ማታ ልቤን ይወጋኛል
ዝም አትበል ተነሥ አመስግን ይለኛል
2.
የለበሰው ልብስ በጠላት ሲገፈፍ
አደባባይ ቆሞ ራቁቱን ሲገፈፍ
አላፈረም በእኔ ቢበዛም መርገሙ
እኔም ዘምራለሁ አላፍርም በስሙ
3.
አጥንቴን ጅማቴን ነፍሴን እያራሰ
ፍቅሩ ልቤን ሞልቶ ከመፍሰስ ደረሰ
አልችልም መቋጠር አልችልም ዝምታ
ባለውለታዬ ስሙ ይክበር ጌታ
4.
ከአቻምና አምና ከአምናም ዘንድሮ
ከትናንቱ ዛሬ ብዙ እጥፍ ጨምሮ
ቃል እስከማጣለት ውለታው በዛብኝ
ሕያዋን ሁላችሁ ተመስገን በሉልኝ።
100%
100%