ምን ይዤ ልቅረብ ከፊትህ
ጌታ ሆይ ደስ ላሰኝህ
ጽድቄ የመርገም ጨርቅ ነው
ብትገልጸው ጉዴ ብዙ ነው
1.
ትምክሕቴ አንተ ነህ የጽድቄ ፍሬ
መቆም አልችልም ፊትህ ደፍሬ
ጌታ የእኔን ነገር ተወት አርግና
በምሕረት እየኝ ዛሬ እንደገና
2.
ስላልተቻለኝ በስሜ መኖሩ
ከኃጢአት ጋር መደራደሩ
በእኔ ምክንያት ስምህ ተሰድቧል
ክፉ ሥራዬ ቤትህን አርክሷል።
3.
ሥራዬ ሁሉ ዊግ የመታው ነው
ሕይወት የማይሰጥ ጣዕም የሌለው
ምን ይፔ ታድያ ልስገድ በፊትህ!
የቱ ነው ላንተ ደስ የሚያሰኝህ?
4.
በአንደበቴ ለውን አማለሁ
ደግሞ እንደገና እሳደባለሁ
በዚያው መልሼ እዘምራለሁ
ዕለት ዕለትም አሳዝናለሁ።