ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #160 / Song #160

የማመልከውን መርጫለሁ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የማመልከውን መርጫለሁ
የሚያዋጣኝን አውቄያለሁ
በብርቱ ክንድ ተደግፌያለሁ
የሚያሳፍረኝ የለም አምናለሁ
1.
በአስተማማኝ እጅ ውስጥ አለሁ
ምንጊዜም ቢሆን በማያሰጋው
በእርሱ ታምኜ እኖራለሁ
ለሕይወቴም ዋስትና አለው
2.
ማነው ከእንግዲህ የሚከሠኝ
ብቸኛ ነህ ብሎ የሚኮንነኝ
እኔስ አባት አለኝ የማይለየኝ
3.
ለህዝብና ለእውነት የሚቆም
ክንደ ብርቱ እስከ ዘላለም
መቼም ቢሆን ጥሎኝ የማያውቅ
ጌታ አለልኝ ተግቶ የሚጠብቅ
4.
ከእንግዲህ ለምን እሰጋለሁ
መሠረቴ ምንጊዜም ፅኑ ነው
ለእውነት ብቻ እቆማለሁ
ማዳኑን ለዓለም አወጃለሁ
5.
በምድር በሰማይ የሚያስተማምን
ለሥጋ ለመንፈስ የሚሆን ተገን
ለሁሉ ሚጠቅም የሁሉ ረዳት
ጌታ የሱስ ነው የኔ አባት
100%
100%