ፍቅር ነው እግዚአብሔር ፍቅር ነው
ፍቅር ነው እግዚአብሔር ፍቅር ነው (፪x)
1.
ኃጢአት አሸፍቶት፡ ጫካ የገባውን
ፀጋውን ተገፎ የተራቆተውን
ወዳለበት ሂዶ ድምጹን ያሰማና
ዳግም ያቆመዋል ያለባብስና
2.
የበደሉን ብዛት መሸከም ላቃተው
ነገር ግራ ገብቶት ለሚወተውተው
ፍቅር ሲጐበኘው ሲሰጠው ምልክት
በእርጋታ ይቀመጣል ይሆናል ባለርስት
3.
ወንድሞቹ ጠልተውት በጉድጓድ ለጣሉት
ከሞቀ ሠልፉ በግፍ ላባረሩት
አፍቃሪው እግዚአብሔር አብሮት ይወጣና
ሰባሳቢ ያደርገዋል ሥፍራ ይሰጠውና
4.
በትልቅ ዋሻ ውስጥ ወስደው ለቀበሩት
ድንጋይ ገጥመውበት አከተመ ላሉት
በሐዘኑ ሰፈር ፍቅር ፈጥኖ ደርሶ
ወገን ያደርገዋል ሟቹን አስነስቶ
5.
5. ዓለሙን በሙሉ እንዲሁ የወደደ
በክርስቶስ በኩል ጥልን ያስወገደ
ፍፁም ቅዱስና ርህሩህ የሆነው
ዘመን የማይሽረው እግዚአብሔር ፍቅር ነው