ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #137 / Song #137

አዋጅ በተራራ መለከት ይነፋ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ወንጌል ላለም ሁሉ በፍጥነት ይስፋፋ
የፍርድ ሰዓት ደርሷል ፍጥረት ሁሉ ይስማ
ጌታችን ይመጣል በክብር በግርማ
1.
የፍጥረት መራወጥ የሁከቱ መብዛት
ውሃ ልክ ሲሞላ የዘመኑ ክፋት
የእውነት መረገጥ ክደት በየሥፍራ
ምፃቱን ያሳያል አዋጅ በተራራ
2.
ለሰማዩ መንግሥት ህዝቡ ይሰናዳ
የዘመን ፍፃሜ መሆኑን ይረዳ
መለከት ይነፋ ከአራቱም ማዕዘን
ከምርኮ ውስጥ ይውጡ የአምላክ ቅዱሳን
3.
ሁሉም ከመኝታው በርግጐ ይነሣ
ፈጥኖ ራሱን ያጽዳ የሕይወቱን አበሳ
የዚህ አለም ኑሮ ሊያልፍ ነው በአፍታ
በክብር ሊገለጽ ነው የጌቶቹ ጌታ
4.
ይብቃን እንነሣ የእንቅልፉ ዘመን
ሌሊቱ ሳይመጣ ፈጥነን እንሥራ አሁን
ይህ ወሳኝ ጊዜ ነው ከእንግዲህ ቸል አንበል
ህይወት ቀልድ አይደለም ለመዳን እንቸኩል
100%
100%